በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ዙሪያ በተደጋጋሚ የሚነሱ ጥያቄዎች

አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት(አተት)/Acute Watery Diarrhea (AWD) ምንድን ነው?
አጣዳፊ ተቀማጥና ትውከት /አተት/ ማለት በተለያዩ ጎጂ ተሕዋስያን አማካኝነት ሊመጡ ከሚችሉ ተላላፊ ከሆኑ በሽታዎች አንዱ ነው፡፡ አተት በፍጥነት የሚዛመትና ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ /የሚጋባ/ በሽታ ነው፡፡ አተት አጣዳፊ የሕዝብ የጤና ችግር ስለሆነ በፍጥነት የመሠራጨት ፀባይ ስላለውና በጊዜው አስቸኳይ ሕክምና ካላገኘ ብዙዎችን ለሞት የሚያደርስ ስለሆነ የበሽታው መጠሪያ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት /አተት/ ይባላል፡፡ እንዲህ ያሉ የጤና ችግሮች አብዛኛውን ጊዜ የሚከሰቱት ብዙ ጥፋት ካደረሰ የሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ በኋላ በሚከተል ቀውስ ሲሆን በወረርሽኝ መልክ ተከስተው የብዙ ሰዎች ሕይወት ሊያጠፉ ይችላሉ፤ አብዛኛውን ጊዜ አተት ተብሎ የሚገለጠው የኮሌራ ወረርሽኝም ሊሆን ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይበጃል፤ አንድ ሰው በአተት ተይዟል ተብሎ የሚጠረጠረው ሰውየው በቀን 3 ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ሲያስቀምጠው ነው፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የአተት በሽታ በወረርሽኝ ደረጃ በሃገራችን ሊከሰት እንደሚችል ነው፤ በመሆኑም ሙሉ መረጃውን ከጤና ጥበቃ ሚኒስትር ባገኘነው መሰረት አቅርበናል አንብቡት፡፡

==ጥያቄ፡- አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት)ማለት ምን ማለት ነው?==

• አተት ማለት በድንገት የሚከሰት አጣዳፊ የተቅማጥ በሽታ ነው።
• የአተት በሽታ መንስኤው የአንጀት በአይን በማይታዩ ተህዋስያን አማካኝንት መመረዝ ነው፡፡
• አተት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በንጽህና ጉድለት ሲሆን
• በሽታው በአብዛኛው ምንም አይንት ምልክት ላያሳይ ወይም
• መጠነኛ ምልክቶች ሊኖሩት ይችላል
• አተት አልፎ አልፎ የከፋ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችል በሽታ ነው፡፡
• ታማሚው ሰው በአፋጣኝ የሕክምና እርዳታ ካላገኘ በሥዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ ይችላል።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ምልክቶች ምን ምን ናቸው ?==

• የአተት በሽታ ዋናው ምልክት በድንገት የሚከሰት ብዛት ያለው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ነው።
• አተት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በተደጋጋሚና አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በማስወጣት የሰውነት ፈሳሽንና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን መጠን ስለሚያዛባ፡
o የሰውነት ድርቀት፣
o የአፍ መድረቅ፣
o የአይን መሰርጎድ፣
o የእንባ መድረቅ፣
o የሽንት መቀነስ፣
o የቆዳ መሸብሸብና
o የእግር መቀረጣጠፍ
• አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ምን ምን ናቸው?==

• አተት በዋናነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአካባቢና የግል ንጽህና መጓደል አማካኝነት ነው።
• በሽታው በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ሲሆን:
• ንጹህ ባልሆኑ እጆች ምግብን ማዘጋጀት፣ ማቅረብና መመገብ፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧና ወዘተ ውሃን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን መጠቀም፣
• ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ ምግቦችን፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን መመገብ ናቸው።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?==

• ሁልጊዜ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ወይም
• በውሃ ማከሚያ ኬሚካል የታከመ ውሃ መጠቀም፤
• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ፤
• የምግብ እቃዎችን በንጹህ ወይም በኬሚካል በታከመ ውሃ ማጠብ እና መጠቀም፣
• መጸዳጃ ቤትን አዘጋጅቶ በአግባቡ መጠቀም፤
• እጅን በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት በንጹህ ውሃና በሳሙና ሳሙና ከሌለ በአመድ ወይም አሸዋ በሚገባ መታጠብ፣

o ከመጸዳጃ ቤት መልስ
o ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
o ምግብ ከማቅረብ በፊት
o ምግብ ከመመገብ በፊት
o ሕጻናትን ካጸዳዱ በኃላ
o ሕጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት
o በበሽታው ለተያዙ ሰዎች እንክብካቤ ካደረጉ በኃላ
o በበሽታው የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በድንገት ከነኩ

• ማንኛውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻን ውሃንና አካባቢን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ፣
• በአተት በሽታ የታመመውን ሰው ልብስ በፈላ ውሃ መቀቀል ወይም በበረኪናና በልብስ ማጽጃ ሳሙና ዘፍዝፎ ማጠብ፣
• በበሽታው የተያዘን ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በመዉሰድ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ናቸው።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ምልክት ሲታይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት ምን ምን ናቸው?==

• በመጀመሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ንጽህናው የተጠበቀ ፈሣሽ ታማሚው ሰው የሚችለውን ያህል መጠጣት ወይም፣
• ህይወት አድን ንጥረ ነገር (ኦ .አር.ኤስ) በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ ወይም በታከመ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ መጠጣት፣
• ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 6 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ የህክምና እርዳታ እስኪገኝ ድረስ መጠጣት፣
• ጡት የሚጠቡ ህፃናት በበሽታው ከተያዙ ጡት ማጥባቱን ከወትሮው ጨመር አድርጎ መቀጠል፣
• ከነዚህ በተጨማሪ በአስቸኳይ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የህክምና ተቋም በመሔድ የህክምና እርዳታ ማግኘት ናቸው፡፡

==ጥያቄ፡ አተት በሽታን እንዴት ማከም ይቻላል?==

• አብዛኛዎቹ ከ80-90 ከመቶ የሚደርሱ የአተት በሽታ ታማሚዎች በተቅማጥ የወጣውን ፈሳሽ በሕይወት አድን ንጥረነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በመተካት ብቻ ይድናሉ፡፡
• ጥቂቶች ከ 10-20 ከመቶ የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ የሰውነታቸውን ፈሳሽ የጨረሱ ታማሚዎች በአፋጣኝ በደም ስር በሚሰጥ ፈሳሽ አማካኝነት መተካት ያስፈልጋቸዋል፡፡
• ታማሚው በአፉ መጠጣት የሚችል ከሆነ በደም ስር የሚሰጥ ፈሳሽ እየወሰደም ሆነ ከወሰደ በኋላ ኦ.አር.ኤስ መጠጣት ይኖርበታል፡፡
• ኦ.አር.ኤስ አተት መከሰቱን ተከትሎ የሚመጣን የሰውነት ፈሳሽ እና ንጥረ ነገሮች መዛባት ለማስተካከል ይረዳል፡፡
• ፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጽኑ ለታመሙ ሰዎች መስጠት በሽታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሄድ፣ የህመሙን ቆይታ ለመቀነስና ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
• አትት በተፈጥሮ የትኛውም የአለማችን ክፍል በብዙ አካባቢዎች የሚገኝ በሽታ ነው፡፡
• አተት በታዳጊ አገሮች፣ የጎርፍ፣ ድርቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጦርነትና የመሳሰሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰቱና ከተከሰቱ በኋላ ሊከሰት ይችላል፡፡
• በድሕነት እና በተለያዩ ምክንያቶች በአንድ አካባቢ ተፋፍገዉ ዎይም ተጨናንቁው በሚኖሩ ሰዎች ላይ በቀላሉ ሊከሰት የሚችል በሽታ ሲሆን፣
• አተት ከቦታ ቦታ በተበከለ ዉሃ እና ምግብ ወይም በበሽታው በተያዙ ሰዎች አማካኝንት ሊዛመት ይችላል፡፡

==ጥያቄ፡ እጅን በሚገባ ለመታጠብ የሚረዱ ሂደቶች ምንምን ናቸው?==

1. እጅን በዉሃ ማርጠብና ሳሙና መምታት፤ሳሙናው አረፋ እስከሚያወጣ ድረስ የእጅን መዳፎች መፈተግ፣
2. የሁለቱንም እጆች መዳፍ በየተራ የሌላኛውን እጅ ጀርባ ላይ ማሸት፣
3. የሁለቱንም እጆች በጣቶች መካከል ያለውን አካል ማሸት፣
4. ጣቶች እንደተጋጠሙ ሁለቱንም እጆች ማሸት፣
5. የሁለቱንም አውራ ጣቶች ዙርያ ማሸትና፣
6. የእጅን መዳፎች ጣቶችን ክብ እየሠሩ ማፋተግ ከዚያም እጅን በዉሃ አለቅልቆ በነፋስ ማድረቅ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ሳሙና በቤት ውስጥ ከሌለ እጅን በአመድ ወይም በአሸዋ አሽቶ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

==ጥያቄ፡ አተት የበሽተኛውን ሰው ሰውነት እንዴት ይጎዳል?==

• የአተት በሽታ አምጭ ተህዋስያን ወደ ጤነኛ ሰው አንጀት ከገባ በኋላ ከጥቂት ሥዓታት – 5 ቀናት (በአብዛኛው ከ 2 – 3 ቀናት) ውስጥ የመጀመሪያ የበሽታው ምልክት ያሳያል፡፡
• አብዛኛዎቹ በአተት በሽታ አምጭ ተህዋስያን የተመረዙ ሰዎች አነስተኛ የሕመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል ወይም ፣
• ምንም አይነት የበሽታ ስሜትላይኖራቸው ይችላል፣
• መጠነኛ የአተት ተቅማጥ በሽታ የሰውነት ድርቀት ላይታይበት ወይም መጠነኛ የሰውነት መጠማት ሊታይበት ይችላል፡፡
• የከፋ ደረጃ ላይ የደረስ የአተት በሽታ የሚከተሉት ልዩ መገለጫዎች ይኖሩታል፡
• በድንገት የሚከሰት ተቅማጥ፣
• መጠነ ብዙ፣ ሕመም አልባ እና ውሃማ (የሩዝ ውሃ የሚመስል) ተቅማጥ፣
• በአብዛኛው ህመሙ እንደጀመረ ማስታወክ ሊኖረው ይችላል፣
• አብዛኛዎቹ ታማሚዎች ትኩሳት አይኖራቸውም ነገር ግን ሕፃናት ላይ ትኩሳት ሊታይባቸው ይችላል፡፡
• ታማሚው በ1 ሥዓት ውስጥ እስከ 1ሊትር ተቅማጥ ሊያስወጣ ስለሚችል የሰውነት ድርቀት በፍጥነት ይከሰታል ፡፡

==ጥያቄ፡ ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ እንዴት ማዘጋት ይቻላል?==

• በቤት ውስጥ ኦ.አር.ኤስ ከሌለ፡ ሕይወት አድን ፈሳሽ እንደሚከተለው ያዘጋጁ;
• ውሃ፣ ጨው እና ስኳር በመጠቀም 1 ሊትር ኦ.አር.ኤስ ለማዘጋጅ፡
• ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የታከመ ውሃ — 1 ሊተር
• ስኳር— ስድስት (6) ሙሉ የሻይ ማነኪያ
• ጨው —- ግማሽ (1/2) የሻይ ማነኪያ
• ውህዱን በሚገባ በማማሰል ስኳሩንና ጨውን ማሟሟት
• ታማሚው ሕክምና ተቋም እስኪደርስ ድረስ ማጠጣት ናቸው፡፡

==ጥያቄ፡ ውሃን በቤት ውሥጥ ማከም የሚቻልው እንዴት ነው?==

• ውሃን በቤት ውስጥ በተለያዩ አማራጭ መንገዶች ለምሳሌ፡ በማፍላት እና ክሎሪን በመጨመር ማከም ይቻላል፡፡
• ዉሃን ማፍላት፡ ውሃን ሙሉ በሙሉ ከተህዋስያን ነፃ ለማድረግ የሚከተሉትን ሒደቶችን መከተል ያስፈልጋል፡፡
o ዉሃው መፋላት ከጀመረ በኋላ ከ 5-10 ደቂቃዎች ያክል መፍላቱን መቀጠል ይኖርበታል
o ወዲያዉኑ አቀዝቅዞ ንጽህናው በተጠመቀ እቃ በማስቀመጥ መጠቀምና
o በምንጠቀምበት ወቅት ዉሃውን ለብክለት ከሚያጋልጡ ነገሮች እና እቃዎች መጠበቅ ናቸው፡፡
• ውሃን በክሎሪን ማከም (ክሎሪኔሽን)፡
o ዓላማው ጎጅና ለበሽታ መንስኤ የሆኑ ተህዋስያንን መግደል ነው፡፡
o ይህንን ውጤት ለማግኘት በቂ የክሎሪን መጠን ውሃው ላይ መጨመር ያስፈልጋል፡፡
o ውሃው የሚያስፈልገው የክሎሪን መጠን ውሃ በካይ የሆኑ ነገሮችን ማቃጠል ወይም ማምከን የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
o ውሃ ከታከመ በኋላ እንዳይበከል ከ0.2 – 0.5 ሚ..ግ. ክሎሪን ዝቃጭ በ 1 ሊትር ውስጥ እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል
o በ1 ሊትር ውሃ የክሎሪን ዝቃጭ ከ0.5 ሚ..ግ. በላይ ከሆነ መጥፎ ሽታና ጥሩ ያልሆነ ጣዕም ሊያስከትል ይችላል፡፡

==የተለመዱ የደፈረሰና ድፍርስ ያልሆነ ዉሃን ለማከም የሚያገለግሉ የክሎሪን አይነቶች ውስጥ የሚከተሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው==

1. ውሃ አጋር (ዋተር ጋርድ)፡

• በ20 ሊትር ክዳን ያለው ንጹህ ጀሪካን ዉስጥ ያልታከመ ውሃ መሙላት
• በዉሃ አጋር ክዳን ሙሉ ዉሃ አጋር ፈሳሽ 20 ሊተር ውሃ ውስጥ መጨመር
• ጀሪካኑን በመክደን ጀሪካኑን በማወዛዎዝ ውሃ አጋሩ እንዲቀላቀል ማድረግ
• ጎጅ ተህዋሲየን እስኪሞቱ ድረስ ለ 30 ደቂቃ መጠበቅ
• ከ 30 ደቂቃ በኋላ ውሃው ለማነኛውም አገልግሎት ዝግጁ ይሆናል
• እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ሌላ ንጹህ የዉሃ ማጠራቀሚያ ዕቃ መገልበጥ ይቻላል
• ብክለትን ለመከላከል ሁልጊዜ የዉሃ ማጠራቀሚያ እቃ መከደን ይኖርበታል
• ወደ ዉሃ ማስቀመጫ እቃ ጆግ ወይም ሌላ መጥለቂያ እቃ መጨመር የለበትም

2. አኳ ታብ (አኳ ታብ):

• 20 ሊተር ያለታከመ ዉሃ ማዘጋጀት
• ዉሃው ድፍርስ ካልሆነ 1አኳ ታብ ኪኒን መጨመር
• ውሃው ድፍርስ ከሆነ መጀመሪያ ዉሃውን በንጹህ ጨርቅ በማጣራት 2 አኳ ታብ ኪኒን መጨመር
• የአኳ ታብ ኪኒ ሙሉ በሙሉ እስኪሟሟ ድረስ መበጥበጥ
• ከ30 ደቂቃ በኋላ ውሃውን ለታለመለት ጥቅም ማዋል ይቻላል

3. ፒዩር (Pur):

• 10 ሊተር ያልተጣራ ውሃ ማዘጋጀት
• መያዣ እቃውን ወይም ሳቼቱን በመቅደድ 10 ሊተር ያልተጣራ ዉሃ የያዘ ባልዲ ውስጥ 1 ሳኬት ፒዩር መጨመር
• ለ 5 ደቂቃ ዉሃዉን ማማሰል
• ዉሃው እስኪጠል እና ቆሻሳው እሰኪዘቅጥ ድረስ መጠበቅ
• በማጥለያ ወይም በንጹህ የጥጥ ጨርቅ ንጹህ ባልዲ ላይ ዉሃውን ማጥለል
• ተህዋስያኑ እስኪሞቱ ድረስ ለ20 ደቂቃ መጠበቅና
• ዉሃውን ለተፈለገው አገልግሎት ማዋል

4. ቢሻንጋሪ (Bishangari)

• 20 ሊተር ያልታከመ ዉሃ ማዘጋጀት
• የቢሻንጋሪ መያዣ እቃ ወይም ሳቼት በመቅደድ 20 ሊተር ዉሃ ውስጥ መጨመር
• ለ 5 ደቂቃ ዉሃውን ማማሰል
• ጠጣር ነገሩ ባልዲ ስር እስኪዘቅጥ ድረስ መጠበቅ
• በማጥለያ ወይም በንጹህ የጥጥ ጨርቅ ላይ ወደ 2ኛው ባልዲ ማጥለልእና
• ተህዋስያኑ እስኪዳከሙ ድረስ ለ 20 ደቂቃ መጠበቅ
• ዉሃውን ለተፈለገው አገልግሎት መጠቀም

5. ዉሃን በፅሐይ ብርሃን ማከም (ሶላር ዲስኢንፌክሽን):

• የዚህ ዉሃን የማከም ዘዴ ኣላማዉ በዉሃ ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉ ጎጅ ተህዋስያንን ዉሃን አፍልቶ በማቀዝቀዝ ወይም ፓስቹራዜሽን ዘዴ መግደል ነው፡፡
• ሶላር ዲስኢንፌክሽን የፅሐይ ብርሀንን አና የፕላስቲክ የዉሃ ጠርሙስን ብቻ በመጠቀም ዉሃን የማከሚያ ዘዴ ነው፡፡
• የፖሊኢታይሌን ጠርሙስ ማለት በአሁኑ ወቅት ዉሃ እና ለስላሳ መጠጦች በማሸግ ለገቢያ የሚ ቀርቡበት የእቃ አይነቶች ናቸው፡፡
• ዉሃን በፅሐይ ብርሃን ማከም ውጤታማ እና ከክፍያ ነፃ የሆነ ውሃን በቤት ውስጥ የማከሚያ መንገድ ነው፡፡
ውሃን በፅሐይ ብርሃን የማከም አስፈላጊ ደረጃዎች:
• የተለያዩ ቀለም የሌላቸው ፕላስቲክ የዉሃ ጠርሙሶችን መሰብሰብና ጠርሙሶችን ማስቀመጫ ስፍራ ማዘጋጀት
• የፕላስቲክ ጠርሙሶችን ላይ ያለ ወረቅት ማንሳትና ማጠብ
• ጠርሙሶቹን ውሃ መሙላት
• በዉሃው ዉስጥ ያለዉን ኦክስጅን መጠን ለመጨመር የጠርሙሶችን ¼ ኛውን መ ሙላትና ለ 20 ሴኮንዶች ከክዳኑ ጋር መበጥበጥ፣
• ጠርሙሶችን እስከ ክዳናቸው መሙላትና መክደን
• በጣም ጭቃማ የሆነና ድፍርስነቱ ከ30 ነቲዩ በላይ የሆነ ዉሃ ለፅሐይ ብርኃን ከመጋለጡ በፊት መጣራት ይኖርበታል
• ዉሃ የተሞሉ ጠርሙሶችን ፅኃያማ ቀን ከሆን ለ 6 ሥዓታት፣ ደመናማ ከሆነ ደግሞ ለ2 ቀናት ያክል ፅኃይ ብርኃን ላይ ማስቀመጥ
• የዉሃ ጠርሙሶችን የቆርቆሮ ጣሪያ ላይ ማስቀመጥ ዉሃው ከፍተኛ ሙቀት እንዲያገኝ ያደርጋል
• ከዚህ በኋላ ዉሃውን በጠርሙሱ ውስጥ ዕያለ ወይም በሌላ ንጹኅ እቃ በመገልበጥ መጠቀም ይቻላል፡፡
ይህንን ዘዴ ለመጠቀም የሚከተሉትን ነጥቦች ላይ ትኩረት ማድረግ ተገቢ ነው ፡
• አንዱ ጠርሙስ ከ 3 ሊተር በላይ ውሃ መሞላት የለበትም
• በጣም ያረጁና የተቦጫጨሩ ፕላስቲክ ጠርሙሶችን አለመጠቀም
• ይህ ዉሃን የማከም ዘዴ ረዘም ላለ ጊዜ ደመናማና ዝናባማ ለሆነ ወቅት አያገለግልም

6. ዉሃን በጠጠር የማጣራት ዘዴ (ስሎው ሳንድ ፊልተራሽን):

• ዉሃን በቀስታ በአሸዋ የማጣራት ዘዴ ዓላማ ጎጅ ተህዋስያንን፣ ድፍርስነትና ከእንሰሳትና ሰው ቅሪት አካል ብክለትን ለመቀነስ ነው፡፡
• የዚህ የማጣራት ሂደት፡ በመጀመሪያ ያልታከመ ዉሃን ማሳለፍ የሚችል አሸዋ የተሞላ ዕቃ ላይ በቀስታ ማፍሰስ እና የተጣራዉ ዉሃ በታች እንዲፈስ ማድረግ ሲሆን፣
• አንድ በትክክል የተዘጋጀ ማጣሪያ የደቃቅ አሸዋ፣የጠጠር ንጣፍና ከማጣሪያ ስር በተቃራኒ አቅጣጫ የተጣራ ዉሃ ወደ ማጠራቀምሚያ የሚፈስስበት ቀዳዳ እና የዉሃዉን ፍሰት መቆጣጠሪያ አካል ይኖሩታል፡፡
• ስሎው ሳንድ ፊልተሬሽን በዝቅተኛ ወጪ መስራትና ለአነስተኛ የውሃ አቀርቦት መጠቀም ይቻላል፡፡
• ዉሃን በዚህ ዘዴ ማጣራት አስተማማኝ ጎጅ ተህዋስያን ማስወገጂያ መንገድ አይደለም ስለዚህ፡
• ዉሃን ከመጠቀም በፊት በማፍላት ወይም ክሎሪን በመጨመር ማከም ተገቢ ነው፡፡

7. ባዮሎጂካል ማጣራት / ባዮ ሳንድ ፊለትረ/:

• የባዮሎጂካል ማጣራት ዘዴ ዓላማ ዉሃን ለቤት ውስጥ አገልግሎት ምቹ ማድረግ ሲሆን
• ዉሃን በቤት ውሥጥ አልፎ አልፎ ለማጣራት የሚያስችል ትንሹ አይነት ስሎው ሳንድ ማጣሪያ ነዉ
• የባዮ ሳንድ ፊልተር ዋና መለያ ባሕሪት ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል፡
o ኢንተር ሪዞርቬር ዞን – ዉሃ ወደ ማጣሪያዉ የሚጨመርበት
o ሳንድ ዋተር ዞን – ይህ ዉሃ ኦክስጂን ወደ ባዮ ሌየር ሲያልፍ አሸዋዉን የሚያረጥብበት ቦታ ነው
o ባዮሎጂካል ዞን- ከላይ ከአሸዋዉ ንጣፍ ከ 5-10 ሳ.ሜ. ላይ የሚሰራ ነው
o የማጣሪያው አሸዋ ጎጂ ጀርሞችን፣ በዉሃ ላይ የሚነሳፈፉ እና ዉሃን በካይ የሆኑ ነገሮችን ያስወግዳል
o በ ስሎው ሳንድ ማጣሪያ የተህዋስያን ባዮሎጂካል ንጣፍ ከ1-2 ሳ.ሜ. ባለው የአሸዋ ንጣፍ ከላይ ይፈጠራል
o ነን-ባዮሎጊካል ዞን- በዚህ የማጣሪያ ክፍል ውስጥ ኦክሲጅን እና ምግብ ስለማያገኙ ሕይዎት ያላቸው ተህዋስያን መኖር አይችሉም
o ግራቭል ዞን- አሸዋዉን በቦታው የሚይዝና የተጣራ ዉሃመዉጫ ቀዳዳ እንዳይዘጋ ይከላከላል
o የማጣሪያ እቃ ከኮንክሪት ወይም ከፕላስቲክ የሚሰራ ሲሆን ለዚሁ ስራ ተብሎ በተዘጋጁ እና በተመረጡ አሸዋና ጠጠር ይሞላል
o የማጣራት ሒደቱ ያለተጣራ ዉሃ ወደ ዉሃ ማጠራቀሚያ መጨመር እና የተጨመረው ዉሃ ቀስ በቀስ ወደ ታች በባዮ ሌየር አልፎ ወደ አሸዋ እና ጠጠር ንጣፎች እየሰረገ ይፈስሳል
o ከዚያ የተጣራው ዉሃ ወደ ዉጭ ማፍሰሻ ቱቦ በመፍሰስ ለአገልግሎት ዝግጁ ይሆናል
==ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ምልክቶች ምን ምን ናቸው ?==

• የአተት በሽታ ዋናው ምልክት በድንገት የሚከሰት ብዛት ያለው አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ነው።
• አተት ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በተደጋጋሚና አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በማስወጣት የሰውነት ፈሳሽንና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን መጠን ስለሚያዛባ፡
o የሰውነት ድርቀት፣
o የአፍ መድረቅ፣
o የአይን መሰርጎድ፣
o የእንባ መድረቅ፣
o የሽንት መቀነስ፣
o የቆዳ መሸብሸብና
o የእግር መቀረጣጠፍ
• አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል።

===ጥያቄ፡ የአተት በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ምን ምን ናቸው?===

• አተት በዋናነት ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በአካባቢና የግል ንጽህና መጓደል አማካኝነት ነው።
• በሽታው በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፍ ሲሆን:
• ንጹህ ባልሆኑ እጆች ምግብን ማዘጋጀት፣ ማቅረብና መመገብ፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧና ወዘተ ውሃን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን መጠቀም፣
• ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ ምግቦችን፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን መመገብ ናቸው።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል?==

• ሁልጊዜ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ወይም
• በውሃ ማከሚያ ኬሚካል የታከመ ውሃ መጠቀም፤
• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ፤
• የምግብ እቃዎችን በንጹህ ወይም በኬሚካል በታከመ ውሃ ማጠብ እና መጠቀም፣
• መጸዳጃ ቤትን አዘጋጅቶ በአግባቡ መጠቀም፤
• እጅን በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት በንጹህ ውሃና በሳሙና ሳሙና ከሌለ በአመድ ወይም አሸዋ በሚገባ መታጠብ፣
o ከመጸዳጃ ቤት መልስ
o ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
o ምግብ ከማቅረብ በፊት
o ምግብ ከመመገብ በፊት
o ሕጻናትን ካጸዳዱ በኃላ
o ሕጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት
o በበሽታው ለተያዙ ሰዎች እንክብካቤ ካደረጉ በኃላ
o በበሽታው የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በድንገት ከነኩ
• ማንኛውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻን ውሃንና አካባቢን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ፣
• በአተት በሽታ የታመመውን ሰው ልብስ በፈላ ውሃ መቀቀል ወይም በበረኪናና በልብስ ማጽጃ ሳሙና ዘፍዝፎ ማጠብ፣
• በበሽታው የተያዘን ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በመዉሰድ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ናቸው።

==ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ምልክት ሲታይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት ምን ምን ናቸው?==

• በመጀመሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ንጽህናው የተጠበቀ ፈሣሽ ታማሚው ሰው የሚችለውን ያህል መጠጣት ወይም፣
• ህይወት አድን ንጥረ ነገር (ኦ .አር.ኤስ) በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ ወይም በታከመ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ መጠጣት፣
• ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 6 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ የህክምና እርዳታ እስኪገኝ ድረስ መጠጣት፣
• ጡት የሚጠቡ ህፃናት በበሽታው ከተያዙ ጡት ማጥባቱን ከወትሮው ጨመር አድርጎ መቀጠል፣
• ከነዚህ በተጨማሪ በአስቸኳይ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኝ የህክምና ተቋም በመሔድ የህክምና እርዳታ ማግኘት ናቸው፡፡

==ጥያቄ፡ አተት በሽታን እንዴት ማከም ይቻላል?==

• አብዛኛዎቹ ከ80-90 ከመቶ የሚደርሱ የአተት በሽታ ታማሚዎች በተቅማጥ የወጣውን ፈሳሽ በሕይወት አድን ንጥረነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በመተካት ብቻ ይድናሉ፡፡
• ጥቂቶች ከ 10-20 ከመቶ የሚሆኑት በከፍተኛ ደረጃ የሰውነታቸውን ፈሳሽ የጨረሱ ታማሚዎች በአፋጣኝ በደም ስር በሚሰጥ ፈሳሽ አማካኝነት መተካት ያስፈልጋቸዋል፡፡
• ታማሚው በአፉ መጠጣት የሚችል ከሆነ በደም ስር የሚሰጥ ፈሳሽ እየወሰደም ሆነ ከወሰደ በኋላ ኦ.አር.ኤስ መጠጣት ይኖርበታል፡፡
• ኦ.አር.ኤስ አተት መከሰቱን ተከትሎ የሚመጣን የሰውነት ፈሳሽ እና ንጥረ ነገሮች መዛባት ለማስተካከል ይረዳል፡፡
• ፀረ-ተህዋስያን መድኃኒቶች በጽኑ ለታመሙ ሰዎች መስጠት በሽታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሄድ፣ የህመሙን ቆይታ ለመቀነስና ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ ለመቀነስ ይረዳል፡፡
ጥያቄ፡ የአተት በሽታ ተጋላጭነትን የሚጨምሩ ነገሮች ምን ምን ናቸው?
• አትት በተፈጥሮ የትኛውም የአለማችን ክፍል በብዙ አካባቢዎች የሚገኝ በሽታ ነው፡፡
• አተት በታዳጊ አገሮች፣ የጎርፍ፣ ድርቅ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ ጦርነትና የመሳሰሉ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ድንገተኛ አደጋዎች ሲከሰቱና ከተከሰቱ በኋላ ሊከሰት ይችላል፡፡
• በድሕነት እና በተለያዩ ምክንያቶች በአንድ አካባቢ ተፋፍገዉ ዎይም ተጨናንቁው በሚኖሩ ሰዎች ላይ በቀላሉ ሊከሰት የሚችል በሽታ ሲሆን፣
• አተት ከቦታ ቦታ በተበከለ ዉሃ እና ምግብ ወይም በበሽታው በተያዙ ሰዎች አማካኝንት ሊዛመት ይችላል፡፡

==ጥያቄ፡ እጅን በሚገገባ ለመታጠብ የሚረዱ ሂደቶች ምንምን ናቸው?==

1. እጅን በዉሃ ማርጠብና ሳሙና መምታት፤ሳሙናው አረፋ እስከሚያወጣ ድረስ የእጅን መዳፎች መፈተግ፣
2. የሁለቱንም እጆች መዳፍ በየተራ የሌላኛውን እጅ ጀርባ ላይ ማሸት፣
3. የሁለቱንም እጆች በጣቶች መካከል ያለውን አካል ማሸት፣
4. ጣቶች እንደተጋጠሙ ሁለቱንም እጆች ማሸት፣
5. የሁለቱንም አውራ ጣቶች ዙርያ ማሸትና፣
6. የእጅን መዳፎች ጣቶችን ክብ እየሠሩ ማፋተግ ከዚያም እጅን በዉሃ አለቅልቆ በነፋስ ማድረቅ ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ፡ ሳሙና በቤት ውስጥ ከሌለ እጅን በአመድ ወይም በአሸዋ አሽቶ መታጠብ ያስፈልጋል፡፡

==ጥያቄ፡ አተት የበሽተኛውን ሰው ሰውነት እንዴት ይጎዳል?==

• የአተት በሽታ አምጭ ተህዋስያን ወደ ጤነኛ ሰው አንጀት ከገባ በኋላ ከጥቂት ሥዓታት – 5 ቀናት (በአብዛኛው ከ 2 – 3 ቀናት) ውስጥ የመጀመሪያ የበሽታው ምልክት ያሳያል፡፡
• አብዛኛዎቹ በአተት በሽታ አምጭ ተህዋስያን የተመረዙ ሰዎች አነስተኛ የሕመም ስሜት ሊኖራቸው ይችላል ወይም ፣
• ምንም አይነት የበሽታ ስሜትላይኖራቸው ይችላል፣
• መጠነኛ የአተት ተቅማጥ በሽታ የሰውነት ድርቀት ላይታይበት ወይም መጠነኛ የሰውነት መጠማት ሊታይበት ይችላል፡፡
• የከፋ ደረጃ ላይ የደረስ የአተት በሽታ የሚከተሉት ልዩ መገለጫዎች ይኖሩታል፡
• በድንገት የሚከሰት ተቅማጥ፣
• መጠነ ብዙ፣ ሕመም አልባ እና ውሃማ (የሩዝ ውሃ የሚመስል) ተቅማጥ፣
• በአብዛኛው ህመሙ እንደጀመረ ማስታወክ ሊኖረው ይችላል፣
• አብዛኛዎቹ ታማሚዎች ትኩሳት አይኖራቸውም ነገር ግን ሕፃናት ላይ ትኩሳት ሊታይባቸው ይችላል፡፡
• ታማሚው በ1 ሥዓት ውስጥ እስከ 1ሊትር ተቅማጥ ሊያስወጣ ስለሚችል የሰውነት ድርቀት በፍጥነት ይከሰታል ፡፡

==ጥያቄ፡ ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ እንዴት ማዘጋት ይቻላል?==

• በቤት ውስጥ ኦ.አር.ኤስ ከሌለ፡ ሕይወት አድን ፈሳሽ እንደሚከተለው ያዘጋጁ;
• ውሃ፣ ጨው እና ስኳር በመጠቀም 1 ሊትር ኦ.አር.ኤስ ለማዘጋጅ፡
• ፈልቶ የቀዘቀዘ ወይም የታከመ ውሃ — 1 ሊተር
• ስኳር— ስድስት (6) ሙሉ የሻይ ማነኪያ
• ጨው —- ግማሽ (1/2) የሻይ ማነኪያ
• ውህዱን በሚገባ በማማሰል ስኳሩንና ጨውን ማሟሟት
• ታማሚው ሕክምና ተቋም እስኪደርስ ድረስ ማጠጣት ናቸው፡፡

==ጥያቄ፡ አተት የታመመ ሰዉ የትዉከት ወይም ተቅማጥ ማቆሚያ መድኃኒቶችን መዉሰድ ይችላሉ?==

• የአተት በሽታ ዋናዉ ሕክምና የወጣዉን ፈሳሽ እና ኤሌክትሮላይት መተካት ነው
• መርዛማ ንጥረ ነገር የያዘው የአንጀት ፈሳሽ ግን መወገድ ይኖርበታል ስለዚህ
• በአተት በሽታ የታመመ ሰው የሚከተሉትን የትዉከት ወይም የየተቅማጥ ማቆሚያ መድሀኒቶችን መውሠድ የለባቸውም፡፡
o ትዉከትን ለማስቆም የሚያገለግሉ (አንቲ – ኤሜቲክ) መድሀኒቶችን
o ተቅማጥን ለማስቆም የሚያገለግሉ (አንቲ – ዲያርያል) መድኃኒቶችን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *